በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አጥፍቶ ጠፊ ​በፓኪስታ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት አደረሰ


ወታደሩ የቦምብ ጥቃት በደረሰበት ሥፍራ ላይ የደረሰውን ጉዳት ሲመረምር
ወታደሩ የቦምብ ጥቃት በደረሰበት ሥፍራ ላይ የደረሰውን ጉዳት ሲመረምር

በሰሜን ምዕራብ ፓኪስታን፣ አንድ አጥፍቶ ጠፊ በፖሊስ ጣቢያ ላይ ባደረሰው ጥቃት 23 ፖሊሶችን ሲገድል 32 አቁስሏል።

የፓኪስታን ባለሥልጣናት እንዳሉት፣ አጥፎቶ ጠፊው ፈንጂ የጫነ መኪናውን በሀገሪቱ ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ በሚገኘው የፖሊስ ጣቢያው ዋና መግቢያ በር ላይ በማቆም ነው ጥቃቱን ያደረሰው። ፍንዳታው በፖሊስ ጣቢያው ህንፃ ላይ ባደረሰው ተፅእኖ፣ ግማሽ ክፍሉ ተደርምሷል።

ፍንዳታውን ተከትሎ በታጣቂዎች እና በጸጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥም ስድስት አጥቂዎች ተገድለዋል።

የፓኪስታን ታሊባን ቡድን ክንፍ ነው ተብሎ የሚታመነው እና በፓኪስታን አዲስ የተመሰረተው 'ተህሪክ ኢ-ጂሃድ' የተሰኘው ታጣቂ ቡድን ለጥቃቱ ሀላፊነት ወስዶ መግለጫ አውጥቷል። መግለጫው አክሎ፣ ታጣቂዎቹ 20 የፖሊስ አባላት መገደላቸውን ቢያመለክትም፣ ቁጥሩ በገለልተኛ አካል አልተረጋገጠም።

ማክሰኞ እለት በደረሰው በዚህ ጥቃት የቆሰሉት የፖሊስ አባላት አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ በመሆኑ፣ የሟቾች ቁጥርል ሊያሻቅብ ይችላል ሲሉ ባለስልጣናት በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

ጥቃቱ የደረሰበት ፖሊስ ጣቢያ የሚገኝበት ደራ ኢስማዔል ካሃን የተሰኘው ከተማ ለአፍጋኒስታን ድንበር ቅርብ ከተማ ሲሆን፣ ለታጣቂው የፓኪስታን ታሊባን ቡድን ምሽግ ሆኖ ያገለግላል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG