ዋሺንግተን ዲሲ —
ምሥራቃዊ አፍጋኒስታን ውስጥ በደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ከሞቱት ሦስት ሰዎች አንዱ፣ ከፍተኛ የክፍለ ሀገር ባለሥልጣን መሆናቸው ተገለፀ።
የምሥራቃዊ ናንጋርሃር ክፍለ ሀገር ዋና ከተማ በሆነችው ጃላላባድ የደረሰው ጥቃት ዒላማ ያደረገውና የገደለውም የሃይማኖታዊ ጉዳዮች ዳይሬክተርና የሀጂ መንፈሳዊ ጉዞ ክፍል ኃላፊ የሆኑትን አብዱላክ ዛሂር ሃቃኒንን እንደሆነም ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
አንድ የክፍለ ሀገሩ መንግሥታዊ ቃል አቀባይ ለቪኦኤ እንደገለፀው፣ ጥቃቱን ያደረሰው አጥፍቶ ጠፊ፣ ወደ ባለሥልጣኑ ተሽከርካሪ በመጠጋት ነው ግድያውን የፈፀመው።
የሃቃኒ ጠባቂ፣ ከሟቾቹ መካከል እንደበርና በፍንዳታው ሌሎች በርካታ ሰዎች እንደቆሰሉም ታውቋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ