በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍጋኒስታን በደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ ፍንዳታ የሞትና የመቁሰል አደጋ ደረሰ


ደቡባዊ አፍጋኒስታን ውስጥ የደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ ፍንዳታ፣ ዘጠኝ ደጋፊዎቹን ጨምሮ አንድ የምክር ቤት ምርጫ ተወዳዳሪን መግደሉ ተነገረ።

ደቡባዊ አፍጋኒስታን ውስጥ የደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ ፍንዳታ፣ ዘጠኝ ደጋፊዎቹን ጨምሮ አንድ የምክር ቤት ምርጫ ተወዳዳሪን መግደሉ ተነገረ። ጥቃቱ የደረሰው፣ ታሊባን የአፍጋኒስታኑ ምክር ቤታዊ ምርጫ የይስሙላ ስለሆነ ተወዳዳሪዎችም ሆኑ ደጋፊዎች ቢሳተፉ ጥቃት አካሂዳለሁ ብሎ ባስጠነቀቀ ማግሥት መሆኑ ነው።

ጥቃቱ ያነጣጠረው የደቡባዊ ሄልማንድ ክፍለ ሀገር ዋና ከተማ በሆነችው በላሽካረጋህ መሆኑን የገለጹት የክፍለ ሀገሩ ፖሊስ ቃልአቀባይ አብዱል ሰላም አፍጋን ለቪኦኤ እንደተናገሩት፣ በአደጋው 15 ሰዎች ቆስለዋል።

ሟቹ ባለሥልጣን ሳለህ ሞሀመድ ለምክር ቤቱ የህግ መምሪያ አባልነት የሚወዳደሩ እንደነበሩም ታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG