በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በካቡል በደረሰ የቦምብ ጥቃት አስር ሰዎች ተገድለዋል

በካቡል አፍጋኒስታን መዲና የፖለቲካ ስብሰባ እየተካሄደ ባለበት ሥፍራ በደረሰ የቦምብ ጥቃት ቢያንስ አስር ሰዎች ተገድለዋል።

በካቡል አፍጋኒስታን መዲና የፖለቲካ ስብሰባ እየተካሄደ ባለበት ሥፍራ በደረሰ የቦምብ ጥቃት ቢያንስ አስር ሰዎች ተገድለዋል።

የከተማይቱ ፖሊስ ፅሕፈት ቤት ቃል አቀባይ ባሲር ሙጃሂድ አንድ ከፍተኛ የፖሊስ አዛዥ የሚገኝባቸው ሥምንት የፀጥታ ኃይል መኮንኖች በዛሬ ጥቃት ከተገደሉት መካከል መሆናቸውን ጠቁሟል።

ከሞቱት መካከል ሲቭሎችም እንዳሉባቸው በመግለፅ የሞቱት ብዛት ከ18 በላይ ሊሆን እንደሚችል የአፍጋኒስታን ሚድያ የፀጥታ ኃይል ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።

እሥላማዊ መንግሥት ነኝ የሚለው አሸባሪ ቡድን ለጥቃቱ ኃላፊነት ውስዷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG