በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳኖቹና የኤርትራ ግንኙነት


የደቡብና የሰሜን ሱዳን ልዑካን ከኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡

ባለፈው ሐሙስ አሥመራ የገባውና በካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትሩ ዶ/ር ዴንግ የተመራው የደቡብ ሱዳን ልዑካን ቡድን አባላት ከፕሬዚዳንት ኢሣያስ ጋር ተገናኝተው አዲሲቷን ደቡብ ሱዳንን በመገንባት ላይ ተሞክሮ መቅሰማቸውን ለመገናኛ ብዙኃን ገልፀዋል፡፡

በሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አል መሃንዳስ ኢብራሂም ማኅሙድ የተመራው የሰሜን ሱዳን ቡድን ደግሞ ባለፈው ሰኞ አሥመራ ገብቷል፡፡

የጉብኝቱ ዓላማ በሁለቱ ሃገሮች መካከል ያለውን የመተጋገዝ ዝምድና ከማዳበር አልፎ በሁለቱ ሃገሮች ዜጎችና በንብረት ላይ ስለሚኖረው ነፃ እንቅስቃሴ ለመፈራረምን እንደሚያካትት የቡድኑ መሪ ገልፀዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ኢሣያስ በሃያኛው የኤርትራ ነፃነት በዓል ምክንያት ከሃገራቸው መገናኛ ብዙኃን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ስለሱዳን እንደተናገሩት የደቡብ ሱዳን ሕዝብ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ሲታገልለት የቆየውን እራሱን የመቻል ጥያቄ ኤርትራ ብትደግፍም ከዚህ የሚሻለው ግን የሰሜንና የደቡብ ሱዳን ሕዝቦች አንድነት በመሆኑ በዚሁ ላይ አተኩራ ስትሠራ መቆየቷን ገልፀዋል፡፡

“በአፍሪካ ቀንድ ሃገሮች መካከል የነበረው መተጋገዝ እየተዳከመ በመምጣቱ በተፈጠረ ክፍተት የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት የሱዳንን ሁኔታ ወደማይሆን አቅጣጫ ወስዶታል” ሲሉ ኢሣያስ አፈወርቂ ተናግዋል፡፡

ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG