በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን የሴቶች መብት ቡድኖች ጥምረት


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

አንድ የሱዳን የሴቶች መብት ቡድኖች ጥምረት፣ በሽግግሩ መንግሥት ህገ-መንግሥት ላይ በሰፈርው መሰረት፣ በመላ የመንግሥት የሥልጣን እርከኖች፣ በክፍላተ-ሃገር አስተዳዳሪነትንም ጭምር ሴቶች ቦታ እንዲያገኙ ጠይቋል።

የሱዳን ሴቶች ባለፈው ዓመት፣ የኡመር አል-ባሽን መንግሥት ባስወገደው አብዮት ውስጥ፣ ትልቅ ሚና መጫወታቸው እውቅና ሊሰጠው ይገባል ሲል፣ ከ10 በላይ የሚሆኑ፣ የፖለቲካና የሲቪል ማኅበራት የሴቶች ቡድኖችን ያቀፈው ጥምረት ጥያቄ አቅርቧል።

የሱድን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ፣ በርካታ ሴቶችን በመንግሥት የፖለቲካና ከፍተኛ የሥልጣን ቦታዎች ላይ ለመሾም የገባውን ቃል፣ መተግበር አለበት ሲሉ፣ የጥምረቱ አባል ሰምያ አሊ ኢሳቅ ባለፈው ረቡዕ ባደረጉት ጋዜጣዊ ጉባኤ አስገንዝበዋል።

በሀገሪቱ ህገ-መንግሥት ላይ በሰፈረው አንቀጽ መሰረት፣ ከመላ የሀገሪቱ የመማክርት መቀመጫዎች፣ 40 ከመቶው ለሴቶች መሰጠት አለበት።

የሱዳን የማስታወቅያ ሚኒስትር ፋይሰል ሙሃመድ፣ ባለፈው ሳምንት በተናገሩት መሰረት፣ የ 13 የክፍላተ-ሀገር አስተዳዳሪዎች የሹመት ጥቆማ ተጠናቋል። ነገር ግን በአስተዳዳሪነት የሚሾሙት ሴቶች ብዛትን አስመልክቶ የሚካሄደው ንግግር ቀጥሏል። ሚስትሩ እንደሚሉት፣ አንዳንድ የፖለቲካ ሃይሎች፣ ሴቶችን በአስተዳዳሪነት መሾም ላይ አልተስማሙም።

XS
SM
MD
LG