በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
በሱዳን በወታደራዊና የሲቪሉ ኃይሎች መካከል ያለው ንግግር መሻሻል ማሳየቱን ምንጮች ገለፁ

በሱዳን በወታደራዊና የሲቪሉ ኃይሎች መካከል ያለው ንግግር መሻሻል ማሳየቱን ምንጮች ገለፁ


ታቃዋሚዎች በሱዳን ካርቱም
ታቃዋሚዎች በሱዳን ካርቱም

ዓለም አቀፋዊ ጫና እየበረታባት ባለችው ሱዳን በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክና ወታደራዊ ግልበጣውን ባካሄዱት መሪዎች መካከል ያለው ንግግር መሻሻል እያሳየ መሆኑን ተዘገበ፡፡

ሮይተርስ ለጠቅላይ ሚኒስትር ቅርበት ያላቸውን ምንጮች ጠቅሶ ትናንት ከካይሮ እንደዘገበው መሻሽሉ የታየው ዩናይትድ ስቴትስ እና የተባበሩት መንግስታት ለመፍትሄው ባሳደሩት ጫና ነው፡፡

ሱዳን 14 አዲስ የልዕልና ምክር ቤት አባላትን በመሰየም ለሽግግር የሚያበቃ አዲስ ተቋም ልትመሰርት የምትችል መሆኑንም ሌሎች ምንጮችን በመጥቀስ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ትናንት ሀሙስ ከወታደራዊ መሪ አብዱል ፈታ አልቡርሃን ጋር በመነጋገር ህገመንግሥታዊ ሥር ዓቱንና የሽግግር ሂደቱን በቦታው እንዲመልሱ ያሳሰቧቸው መሆኑን ተመልክቷል፡፡

ትናንት ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንቶኒ ብሊነክን ጋር የተነጋገሩት አልርቡሃን አዲሱን መንግሥት በፍጥነት በመመስረቱ አስፈላጊነት ላይ የተስማሙ መሆኑን የአልቡርሃን ቢሮ መግለጹን ሮይተር ዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG