በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተቃውሞ ሰልፍ በሱዳን


ፎቶ ፋይል፦ የተቃውሞ ሰልፍ ካርቱም፤ ሱዳን ሚያዝያ 6/2022
ፎቶ ፋይል፦ የተቃውሞ ሰልፍ ካርቱም፤ ሱዳን ሚያዝያ 6/2022

በብዙ ሽዎች የተቆጠሩ ሱዳናውያን ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል። ሰልፉ የተጠራው ባለፈው ጥቅምት ወር የተካሄደውን እና ፖለቲካዊ ትርምስ ውስጥ የከተታትን እና የምጣኔ ሀብት ቀውሱን ያባባሰውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት በመቃወም መሆኑን አሶሽየትድ ፕሬስ ዘግቧል።

ሲቪላዊ አስተዳደር እንዲመሰረት በተከታታይ ሰልፍ እየወጡ የሚጠይቁት ተቃዋሚዎች በገዢዎቹ ጀነራሎች ላይ ግፊት ማድረጋቸውን ቀጥለዋል። መፈንቅለ መንግሥቱ ለሠላሳ ዓመታት በቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦመር አል በሽር አፋኝ አገዛዝ ስር በዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተገልላ የቆየችውን ሀገር የዲሞክራሲ ሽግግር ሂደት ገትቶታል።

እአአ በ2009 ሚያዝያ ወር በተነሳው ህዝባዊ አመጽ አልበሽርንና እስላማዊ አስተዳደራቸውን የጦር ኃይሉ ከስልጣን ያስወገደ ሲሆን የዲሞክራሲ ሽግግር ሂደቷ መዳከሙን እንደቀጠለ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG