በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቱኒዚያ ባሕር ዳርቻ 13 ሱዳናውያን ሕይወታቸውን አጡ


ፎቶ ፋይል፦ አፍሪካ ፍልሰተኞች ወደ ጣሊያን ለመሻገር በቱኒዚያ ባህር ዳርቻ በበረት የተሰራ ጀልባ ተሳፍረው እየተጓዙ፤ ሳፋክስ፣ ቱኒዚያ እአአ ሚያዚያ 27/2023
ፎቶ ፋይል፦ አፍሪካ ፍልሰተኞች ወደ ጣሊያን ለመሻገር በቱኒዚያ ባህር ዳርቻ በበረት የተሰራ ጀልባ ተሳፍረው እየተጓዙ፤ ሳፋክስ፣ ቱኒዚያ እአአ ሚያዚያ 27/2023

በቱኒዚያ ባሕር ዳርቻ ይጓዙበት የነበረው ጀልባ ሰጥሞ አሥራ ሶስት ሱዳናውያን ፍልሰተኞች ሲሞቱ፣ ሃያ ሰባት የሚሆኑት ደግሞ የደረሱበት አልታወቀም ሲል የፍርድ ቤት ቃል አቀባይን ጠቅሶ የኤኤፍፒ ዜና ወኪል ዘግቧል።

ሞናስትር በተባለችው የባሕር ዳርቻ ከተማ በሚገኝ ፍ/ቤት ቃል አቀባይ የሆኑት ፋሪድ ቤን ጃ እንዳሉት፣ 42 ከሚሆኑት ፍልሰተኞች ውስጥ እስከ አሁን በሕይወት ተርፈው የተገኙት ሁለት ብቻ ናቸው።

ምርመራ መጀመሩን የገለጹት ቃል አቀባዩ፣ ፍልሰተኞቹ “የሕገ ወጥ አስተላላፊዎች ሰለባ ወይም በሕገ ወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ ለመሻገር በዝግጅት ላይ ያለ ወንጀለኛ ቡድን አባላት ሊሆኑ ይችላሉ” ብለዋል።

ሰለባዎቹ በጦርነት ከምትታምሰው ሱዳን የመጡና በተመድ የፍልሰተኞች ድርጅት በጥገኝነት ጠያቂነት የተመዘገቡ መሆናቸውን ሪፖርቱ ተቁሟል።

ይጓዙበት የነበረው ጀልባ ከተሰባበሩ ብረቶች እንደነገሩ የተሠራ እንደነበር በተደረገው የመጀመሪያ ደረጃ ምርመራ መታወቁ ተገልጿል።

የጠፉትን ፍልሰተኞች ፍለጋው መቀጠሉም ታውቋል።

ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ብቻ ከ2ሺሕ 270 ፍልሰተኞች በላይ በሜዲትሬንያን ባሕር ላይ ሕይወታቸውን አጥተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG