በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን የሽግግር ወታደራዊ መማክርት መንገዶች እንዲከፈቱ ጠየቀ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የሱዳን የሽግግር ወታደራዊ መማክርት መንገዶቹ አሁኑኑ እንዲከፈቱና መሰናክሎቹ እንዲነሱ የጠየቀ ቢሆንም የሱዳን የተቃውሞ መሪዎች ካርቱም ውስጥ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጉን እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

የተቃውሞውን እንቅስቃሴ የሚመራው የሱዳን ባለሙያዎች ማኅበር አዲሱ የሽግግር ወታደራዊ መማክርት ሥልጣኑን ለሲቪል መንግሥት እንዲያስረክብ ለማስገደድ ሲሉ ተከታዮቻቸው ዛሬ በመቀመጥ አድማው እንዲቀጥሉ ጥሪ አድርገዋል። በመዲናይቱ ካርቱም ዛሬ ሰልፍ እንዲደረግ በመጪው ሀሙስ ደግሞ ህዝባዊ መሰባሰብ እንዲኖር ማኅበሩ ጥሪ አድርጓል።

ተቃዋሚዎቹ ትላንት ካርቱም ውስጥ ዋናው የተቃውሞ ቦታቸው በሆነው ወታደራዊ ጽ/ቤት አካባቢ ባሉት መንገዶች ላይ ኬላዎች መሥርተው ሲቆጣጠሩ ታይተዋል። የሱዳን የሽግግር ወታደራዊ መማክርት መንገዶቹ አሁኑኑ እንዲከፈቱና መሰናክሎቹ እንዲነሱ አሳስቧል።

የሱዳኑ ወታደራዊ ም/ቤት ማስጥንቀቅያ ያወጣው ሥልጣን ለሲቪል መንግሥት አላስረክብም በማለቱ ከተቃዋሚዎቹ ጋር ያደረገው ውይይት በተቋረጠ ማግሥት ነው።

ግብፅ የሱዳን ሁኔታን በሚመለከት አስቸኳይ የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔን ለማስተናገድ መዘጋጀትዋ ተገልጿል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG