በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን ወታደራዊ አውሮፕላን ተከስክሶ 46 ሰዎች ሞቱ


ካርቱም እና ኦምዱርማን፣ ሱዳን
ካርቱም እና ኦምዱርማን፣ ሱዳን

በሱዳን ዋና የመዲናዋ መንትያ ከተማ ኦምዱርማን ወታደራዊ አየር ማረፊያ አቅራቢያ በሚገኝ የመኖሪያ መንደር አካባቢ፤ የጦር አውሮፕላን ተከስክሶ 46 ሰዎች መሞታቸውን፤ የኻርቱም የመንግሥት ብዙኀን መገናኛ ቢሮ የገለጸ ሲሆን ከሟቾቹ መካከል አንድ ከፍተኛ የጦር አዛዥ እንደሚገኙ የወታደራዊ ምንጮች ዘግበዋል።

አደጋው የደረሰው ትላንት ማክሰኞ ማምሻውን በሰሜናዊ ኦምዱርማን በዋዲ ሲዳይና ወታደራዊ አየር ማረፊያ አቅራቢያ ነው። የሱዳን ጦር በአደጋው ብዙ ወታደራዊ አባላት እና ሲቪሎች መሞታቸውን ቢገልጽም ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል።

አውሮፕላኑ የተከሰከሰው በቴክኒክ ችግር ሊሆን እንደሚችል ወታደራዊ ምንጮች ገልጸዋል። የሱዳን መገናኛ ጽሕፈት ቤትም በአደጋው ዐስር ሰዎች ቆስለዋል ብሏል።

ከሟቾቹ መካከል ከዚህ ቀደም በመላው ኻርቱም የሰራዊቱ ከፍተኛ አዛዥ ሆነው ያገለገሉት የኻርቱም ሜጀር ጄነራል ባህር አሕመድ እንደሚገኙበት የወታደራዊ ምንጮቹ አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG