በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን የፖለቲካ ምኅዳሩ ለሴቶች እንዲከፈት ጥሪ ቀረበ


የሱዳን የጦር ሰራዊት እና ተቃዋሚ መሪዎች በቅርቡ የደረሱትን ሥልጣን የመጋራት ስምምነት ተግባራዊ ማድረግ ሲጀምሩ የፖለቲካ ምኅዳሩን ለሴቶች እንዲከፍቱ በጉዳዩ የሚንቀሳቀሱ ተሟጋቾች ጥሪ አቀረቡ።

ሱዳን እንደ ነፃ ሀገር ባሳለፈቻቸው ስድሳ ሦስት ዓመታት ውስጥ በአብዛኛው ሴቶች በባህላዊ ምክንያቶችና በሌሎችም ገደቦች ምክንያት በፖለቲካ ተሳትፎ ሳይኖራቸው ቆይተዋል።

በተለይም በቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አልበሺር የሰላሳ ዓመታት አገዛዝ በህዝባዊ ጉዳዮች እንዳንሳተፍ ተገልልለን፣ ተከልክለን ኖረናል ብለው ያማርራሉ።

ባለፈው ሳምንት ወተደረሰው የሥልጣን መጋራት ስምምነት ባመሩት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ሴቶች እንዲሳተፉ በመቀስቀስ ከረዱት፣ የሴቶች መብት ተሟጋቾች አንዷ ማናል በሽር ሴቶች መብታቸው እንዲከበር ድምፃቸውን የሚያሰሙበት ጊዜው አሁን ነው ብለዋል።

የሱዳን የሥልጣን መጋራት ስምምነት ቢያንስ አርባ ከመቶው የምክር ቤት መቀመጫ በሴቶች መያዝ እንዳለበት አስቀምጧል። ስምምነቱ ባፋጣኝ ተግባራዊ እንዲደረግ የሴቶች መብት ተሟጋቾቹ አሳስበዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG