በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን ውጊያው ተፋፍሞ ቀጥሏል


 ፎቶ ፋይል፦ በካርቱ፣ ሱዳን
ፎቶ ፋይል፦ በካርቱ፣ ሱዳን

· ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የጦር ወንጀል ክሡን አስተባብሏል

በሱዳን፣ ለሦስት ወራት የቆየው ጦርነት ተፋፍሞ፣ ትላንት እሑድ፣ መዲናዋ ካርቱም ውሎዋን በአየር ስትደበደብ፣ በምዕራብ ዳርፉር ደግሞ ከባድ ውጊያ እንደነበር ተገልጿል።

የጦር ሠራዊቱ የውጊያ ጄቶች፣ በምሥራቃዊ እና ሰሜናዊ ምዕራብ ካርቱም የሚገኙ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን መደቦች ሲደበድቡ ውለዋል። ፈጥኖ ደራሽ ኀይሉ በበኩሉ፣ የአየር መቃወሚያ መተኮሱን፣ የዐይን ምስክሮች ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል።

በሰሜናዊ ምዕራብ የመዲናዪቱ ክፍል በደረሰ ፍንዳታ፣ አምስት ሰዎች ሲሞቱ፣ 17 የሚኾኑቱ ደግሞ ቆስለዋል።

የፈጥኖ ደራሽ ኀይሉ፣ በካርቱም የሚገኘውን ትልቁን ወታደራዊ ሆስፒታል በድሮኖች እንደ ደበደበ የዐይን ምስክሮች ተናግረዋል። ቅዳሜ ዕለት በተፈጸመ ተመሳሳይ ጥቃት፣ አምስት ሰዎች ሲሞቱ፣ 22ቱ ደግሞ ቆሰለዋል፤ ተብሏል።

28 የሚደርሱ፣ አረብ ያልኾኑ የማሳሊት ጎሣ አባሎችን በጅምላ ገድሏል፤ ሲል፣ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቹ ‘ሂውማን ራይትስ ዎች’ ያወጣውን ሪፖርት፣ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ውድቅ አድርጓል። በተያያዘም ኃይሉ፥ ሚስተሪ የተሰኘችውን ከተማ ሙሉ ለሙሉ በማውደምም ተከሧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG