በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“በሱዳን የቀጠለው ብጥብጥ እስከ ጥቅምት 1 ሚሊዮን ሰዎች ለስደት ይዳርጋል” ተመድ


የሱዳን ጦር ተሽከርካሪዎች በካርቱም ጎዳና ላይ፣ ሱዳን
የሱዳን ጦር ተሽከርካሪዎች በካርቱም ጎዳና ላይ፣ ሱዳን

በሱዳን እየተባባሰ ያለው ውጊያ እስከ ጥቅምት ወር ድረስ ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎችን ለስደት መዳረጉ አይቀርም የሚል ስጋት እንዳለ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል፡፡

ይህ ነው የሚባል መሻሻል ሳያሳይ ለአስር ወራት የቀጠለው ውጊያ የከፋው በዋና ከተማዪቱ ካርቱም ሲሆን የፈጥኖ ደራሹ ጦርና የአረብ ሚሊሺያዎች፣ አረብ ያልሆኑ ጎሳዎችን በሚያጠቁበት በምዕራብ ዳርፉር ክልልም መባባሱን የአካባቢው መብት ተሟጋቾችና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ትናንት ማክሰኞ አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ጥቃት የሸሹት ብዙዎቹ አምልጠው ወደ ምስራቅ ቻድ መሰደዳቸው ተመልክቷል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ረዳት ዋና ጸሀፊ ራውፍ ማዙ ጀኔቭ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “በስድስት ወራት ውስጥ አንድ መቶ ሺህ ሰዎች ወደቻይ ሰደዳሉ ስንል ነበር፡፡ “አሁን ግን ቻድ ያሉ ባልደረቦቻችን ቁጥሩን ከልሰው ወደ 245 ሺህ ከፍ አድርገውታል”ብለዋል ዋና ጸሀፊው፡፡

የዛሬውን የሙስሊሞች የኢድ አድሃ በዓል ምክንያት በማድረግ ተፋላሚዎቹ የጦር ሠራዊቱ መሪ ጀኔራል አልቡርሃን እና የፈጥኖ ደራሹ መሪ ዳጋሎ የተናጠል ተኩስ አቁም አውጀዋል፡፡

እንደተባበሩት መንግሥታት መረጃ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ከ3ሺ በላይ ሰዎች ሲገደሉ 2.5 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ ተፈናቅለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG