በተኩሱ ምክንያት ድርድሩ ለ72 ሰአታት ይቋረጣል ሲሉ ጄኔራል ዐብደል ፋታሕ ዐል-ቡርሀን ዛሬ አስታውቀዋል። ግጭቱ የተነሳው ተቃዋሚዎቹ በመዲናይቱ ዋና መንገዶች ላይ የተከልዋቸውን መሰናክሎች አናነስም በማለታችው ነው በማለት ተጠያቂ አድርገዋቸዋል።
መሰናክሎቹ ባለፈው ወር የተተከሉት ተቃዋሚዎቹ የመቀመጥ አድም ባደርጉበት ወቅት ነው። ተቃውሞው ከሰላማዊ ሰልፍ አድጎ የረዥም ጊዜ አምባገነን መሪ የነበሩትን ኡማር አልባሽርን ከሥልጣን ወደ ማስወገድ አደገ።
ወታደራዊው ኃይል የባሽርን የ30 ዓመታት አገዛዝን ያከተመው እአአ ባለፈው ሚያዝያ 11 ቢሆንም ሥልጣኑን ለሲቪል መንግሥት ማስረከብ አለበት በሚል የመቀመጡ አድማ እንደቀጠለ ነው፤ መሰናክሎቹም አልተነሱም።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ