በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር በኢትዮጲያ ጉብኝት ላይ ናቸው።


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሌተና ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሌተና ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን

የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ጀነራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ለሁለት ቀናት ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የሱዳኑ የሽግግር መሪ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር ሆነው የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎብኝተዋል ፥ ሊሎችንም የልማት ፕሮጄክቶች እንደሚጎበኙ ተገልጿል።

ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን በኢትዮጲያ ቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር የሁለቱን ሃገሮቻቸውን ግንኙነት በማጠናከር ላይ ያተኮሩ ውይይቶች እንደሚያደርጉ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ አመልክቷል ።

XS
SM
MD
LG