በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሱዳን ውስጥ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ተደርጎ መክሸፉን የጦር ሰራዊቱ አስታወቀ


ፎቶ ፋይል፦ ኦማር አል በሽር
ፎቶ ፋይል፦ ኦማር አል በሽር

የጦር ሰራዊቱ ዛሬ ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ ሱዳንን እአአ በ2019 የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦማር አል በሽር ከሥልጣናቸው ከተወገዱበት ጊዜ ጀምሮ እያስተዳደራት የሚገኘው የሲቪል እና የጦር ሰራዊት ጥምር ምክር ቤት የተቃጣውን የግልበጣ ሙከራ አክሽፈናል ሲል ነው ያስታወቀው።

አንድ የገዢው ምክር ቤት ሲቪል አባል ትናንት ሌሊት ላይ ተሞክሮ የነበረው ግልበጣ እንዳይሳካ ተደሩጓል አሁን ሁኔታው በቁጥጥር ሥር ውሏል ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ተጠርጣሪዎቹን የመመርመር ሂደት ይጀመራል ሲሉ ቃል አቀባዩ መሃመድ አል ፋኪ ሱሌይማን መናግራቸውንም ሮይተርስ ጠቅሷል።

ሉዓላዊ ምክር ቤት ተብሎ የሚጠራው እና ጠንካራ ባልሆነ የወታደራዊ እና ሲቪላዊ አካላት ስምምነት የተመሰረተው ገዢው አካል አልበሽር ከተወገዱ ጀምሮ ሀገሪቱን እያስተዳደረ ነው ። እአአ በ2024 (ከሶስት ዐመት በኋላ ማለት ነው) ነጻ ምርጫ ለማካሄድ ዕቅድ አውጥቷል።

የሉዓላዊው ምክር ቤት ሊቀ መንበር የጄኔራል አብደልፈታህ አል ቡርሃን አማካሪ ለመንግሥታዊው ሱና የዜና አገልግሎት በሰጡት መግለጫ

"የጦር ሰራዊቱ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውን አክሽፏል ፥ አሁን ሁኔታው ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ሥር ውሏል” ብለዋል።

ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ የመንግሥት ባለሥልጣን መፈንቅለ መንግሥት ሞካሪዎቹ ኡምዱርማን የሚገኝ የመንግሥት የራዲዮ ጣቢያ ለመቆጣጠር ሞክረው ነበር ብለዋል። በጉዳዩ የተሳተፉትን የተወሰኑ ሰዎች ለመያዝ ርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል በሱና ዘገባ መሰረት በድርጊቱ አሉበት የተባሉት በሙሉ ተይዘዋል።

የሉዓላዊ ምክር ቤቱ ታማኝ ክፍለ ጦሮች ካርቱምን ከኡምዱርማን የሚያገናኘውን ድልድይ በታንክ አጥረውት እንደነበር አንድ የዐይን ምስክር መግለጻቸውን ሮይተር አክሎ አመልክቷል።

የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤቱን መሪዎች የሚፈታተን ሁኔታ ሲገጥማቸው ይህ የመጀመሪያ ጊዜ እንዳልሆነ የጠቀሰው የሮይተርስ ዘገባ ካሁን ቀደምም በአልበሽር ደጋፊዎች የተደረጉ የግልበጣ ሙከራዎችን ደርስንባቸው፣ አክሽፈናቸዋል ማለታቸውን አውስቷል።

ባለፈው ዓመት የሱዳን ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሃምዶክ በዋና ከተማዋ ካርቱም ወደመስራያ ቤታቸው በአጀብ ሲጓዙ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው እንደነበር ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG