ዋሺንግተን ዲሲ —
ሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ፈብሪካ ላይ በደረሰ ፍንዳታ ብዛት ያላቸው ሰዎች ተጎድተዋል። መጀመሪያ ላይ በወጡ ዘገባዎች መሰረት ጋዝ የጫነ መኪና ላይ በደረሰ ቃጠሎ ነው ፍንዳታው የደረሰው።
ሱዳን ውስጥ በበቅርብ ወራት በኢንዱስትሪዎች ላይ በተደጋጋሚ አደጋ እየደረሰ መሆኑ ተስተውሏል። መነሻው የጤና እና የደኅንነት ደምቦች ደካማነት ነው የሚለው ስጋት ጨምሯል።