ዋሺንግተን ዲሲ —
የሽግግሩ ወታደራዊ መማክርት በበኩሉ የፖለቲካ እስረኞችን ለመፍታት መስማማቱን የኢትዮጵያው ልዩ ልዑክ አምባሳደር ማሕሙድ ድሪር ትላንት ካርቱም ላይ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
“የነፃነትና የለውጥ ውኅደት የህዝባዊ አልታዘዝ ባይነትነት እንቅስቃሴን ከዛሬ አንስቶ ለመተው ተስማምቷል” ሲሉ አምባስደር ማሕሙድ ድሪሪ አስታውቀዋል። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ባለፈው ሳምንት ሱዳንን ከጎበኙበት ጊዜ አንስቶ አምባሳደር ማሕሙድ ድሪር ሲሸመገሉ ቆይተዋል።
ሁለቱም ወገኖች የሀገሪቱን ሥልጣን ለሲቪል አስተዳደር ስለማስረከብ ጉዳይም ንግግር ለመቀጠል ተስማምተዋል ይላሉ አምባሳደሩ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ