በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን ሰላም


የኢትዮጵያ ልዩ ልዑክ ማሕሙድ ድሪሪ
የኢትዮጵያ ልዩ ልዑክ ማሕሙድ ድሪሪ

የሱዳን የተቃውሞ መሪዎች አድማዎችንና የህዝባዊ አልታዘዝ ባይነትን ካቆሙ በኋላ የንግድ መደብሮች ተከፍተው መኪኖች በመዲናይቱ ካርቱም እየተሽከረከሩ ናቸው።

የተቃውሞ መሪዎቹና የሀገሪቱ ወታደርዊ ገዢዎች ሱዳንን ወደ ሲቪል አስተዳደር ለመመለስ ዓላማ ንግግር ለመቀጠል ተዘጋጅተዋል።

የረዥም ጊዜ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት የነበሩት ኡመር አልባሽር ባለፈው ሚያዝያ ወር ከሥልጣን ከተወገዱ ወዲህ ሀገሪቱን እየተቆጣጠረ ያለው ወታደራዊ መማክርት የፖለቲካ እስረኞችን ለመፍታት መስማማቱን የኢትዮጵያ ልዩ ልዑክ ማሕሙድ ድሪሪ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በገልፀው መሰረት ሁለቱ ወገኖች የሽግግር ጊዜ ገዢ ካውንስል ምስረታን ባካተቱ የተቀሩ ነጥቦች ላይ ንግግር ለመቀጠል ተስማምተዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ በበኩልዋ ነባር ዲፕሎማት ዶናልድ ቡት ልዩ የሱዳን ልዑክ እንዲሆኑ ሰይማለች። ቡት በኦባማ አስተዳደር ወቅትም የሱዳንና የደቡብ ሱዳን ልዩ ልዑክ ሆነው አገልግለዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ክፍል ረዳት ሚኒስትር ቲቦር ናዥ ለፖለቲካዊ ቀውሱ መፍተኄ ለመፈለግ ሲሉ የሽግግር ወታደራዊ መማክርት መሪዎችንና ሲቪል ተቃዋሚዎችን ለማበረታታት ካርቱም ይገኛሉ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG