በሌላ በኩል ደግሞ በተመሣሣይ ጊዜ ደቡብ ሱዳን የጦር ሠራዊት አዝምታ ከያዘችው የከርሰምድር ዘይት አምራች አካባቢው ቁልፍ ከተማ ሄግሊጅ ወታደሮቿን እንድታስወጣ ግፊት ለማሣደር ኻርቱም ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻም ከፍታለች፡፡
ፕሬዚዳንት በሽር ለአንድ የደጋፊዎቻቸው ቡድን ባደረጉት ንግግር እንግዲህ ዋነኛው ግባቸው የደቡብ ሱዳኑን ገዥ ፓርቲ የሱዳን ሕዝብ አርነት ንቅናቄን በኃይል ማስወገድ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ጦርነት አይቀሬ መሆኑን አስረግጠው በተናገሩበት ኻርቱም ላይ በተደረገ ሰልፍ ላይ “ወይ እኛ ጁባ እንገባለ፤ ወይ እነርሱ ኻርቱም ይገባሉ” ብለዋል፡፡
አልበሽር “ደቡብ ሱዳንን ነፃ አወጣለሁ” ከማለታቸውም ሌላ የደቡብ ሱዳኑን ገዥ ፓርቲ - ኤስፒኤልኤምን “ተባዮች” እያሉ ዘልፈዋል፡፡
ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ