በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አል-ቡርሃን ተፋላሚያቸውን ዳጋሎንና ኀይላቸውን በጦር ወንጀል ከሠሡ


ካርቱም፣ ሱዳን
ካርቱም፣ ሱዳን

የሱዳን ጦር ሠራዊት አዛዥ ጄነራል አብደል ፋታሕ አል-ቡርሃን፣ ዛሬ ሰኞ፣ በቴሌቪዥን ባደረጉት ንግግር፣ ተቀናቃኛቸውን የፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ኀይል፣ በጦር ወንጀለኝነት ከሠዋል።

በአል-ቡርሃንና በፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ኀይሉ አዛዥ ጄነራል ሞሐመድ ሃምዳን ደጋሎ መካከል የነበረው ውጥረት ወደ ግጭት አምርቶ፣ ባለፈው ሚያዝያ ወር፣ በመዲናዋ ካርቱም ውጊያ ሲጀምሩ፣ ሀገሪቱ ወደ ትርምስ ውስጥ ገብታለች፡፡

የጦር ወንጀል እየፈጸሙ ዴሞክራሲን እንዴት ማምጣት ይቻላል?”

አል-ቡርሃን፣ ከረጅም ጊዜ በኋላ፣ የሱዳን ሠራዊት ቀንን አስመልክቶ፣ በአገሪቱ ቴሌቭዥን ቀርበው ባደረጉት ንግግር፣ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉንና ሐምዳን ደጋሎን፣ “ዴሞክራሲን መልሶ ለማምጣት በሚል የመብት ጥሰት ፈጽመዋል፤” ሲሉ ከሠዋል።

አያይዘውም፣ “የጦር ወንጀል እየፈጸሙ ዴሞክራሲን እንዴት ማምጣት ይቻላል?” ሲሉ ጠይቀዋል።

የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቱ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሁለቱም ወገኖች መጠነ ሰፊ የጦር ወንጀል ፈጽመዋል፤ ሲል ይከሣል። ሲቪሎችን ኾን ብሎ ገድለዋል፤ የተስፋፋ ጾታዊ ጥቃትም ፈጽመዋል፤ ሲል፣ የመብቶች ተሟጋች ድርጅቱ፣ 56 ገጾችን በያዘው ሪፖርቱ ከሧል።

እ.አ.አ በ2000 መጀመሪያ ላይ፣ የዘር ማጥፋት በተፈጸመባት ዳርፉር፣ ግጭቱ ወደ ጎሣ ተኮር ጥቃት ተቀይሮ፣ የፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ኀይሉ እና ተባባሪው የአረብ ሚሊሺያ፣ በምዕራብ ዳርፉር፥ ጥቁር አፍሪካውያንን ዒላማ ያደረገ ጥቃት ፈጽመዋል፤ ሲሉ፣ የተመድ ባለሥልጣናት እንደ ከሠሡ፣ የአሶሺዬትድ ፕረዝ ዘገባ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG