በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ አዛዥ የመጨረሻ ጉብኘት በኬንያ


የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት አዛዥ ጄነራል ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት አዛዥ ጄነራል ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት አዛዥ ጄነራል ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ ሀገር ውስጥ ላለው ጦርነት የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ሚደረገው የአካባቢው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ዙሪያ ትናንት ረቡዕ ከኬንያው መሪ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ናይሮቢ ውስጥ ተገናኝተው መክረዋል፡፡

በሚያዝያ አጋማሽ ላይ በፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት እና በሱዳን ጦር መካከል ከፍተኛ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ሰሞኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ውጭ አገር የተጓዙት መሀመድ ሃምዳን ዳግሎን ስትቀበል ኬንያ የመጨረሻዋ የምስራቅ አፍሪካ ሀገር መሆኗን ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡

ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ከዳግሎ ጋር ውይይት ሲያደርጉ የሚያሳዩ ምስሎችን ኤክስ ላይ አስፍረዋል፡፡ ሩቶ ከምስሎቹ ጋር ባስተላለፉ መልዕክትም ”ኬንያ ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት እና ዳጋሎ"የሱዳንን ግጭት በውይይት ለማስቆም" ላሳዩት ቁርጠኝነት ታደንቃለች ብለዋል፡፡

በመካሄድ ላይ ያለው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ውይይት በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም የሚያስገኝ ፖለቲካዊ መፍትሄ ማምጣት አለበት

"በመካሄድ ላይ ያለው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ውይይት በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም የሚያስገኝ ፖለቲካዊ መፍትሄ ማምጣት አለበት" ሲሉም ሩቶ አክለዋል።

በጅቡቲ የሚገኘው የስምንት ምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ህብረት ወይም የልማትና በይነ መንግስታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) በዳግሎ እና በተቀናቃኛቸው የሱዳን ጦር አዛዥ አብዱልፈታህ አል ቡርሃን መካከል ውይይት ለማድረግ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እያደረገ መሆኑ ተመልክቷል፡፡።

በግምት ከ12,000 በላይ ሰዎችን ገድሏል ስለሚባለው እና ሚሊዮኖች እንዲሰደዱ ያስገደደውን ግጭት ለማስቆም በሚቻልበት ሁኔታ ሁለቱ ተዋጊዎቹ ጄኔራሎች እስከዛሬ ፊት ለፊት አልተገናኙም ሲል የኤ ኤፍ ፒ ዘገባ አመልክቷል፡፡

ዳግሎ በአህጉራዊ ጉብኝታቸው ጅቡቲ፣ ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳን የጉበኙ ሲሆን የሱዳኑን ግጭት ለማስቆም ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጦርነቱ ምክንያት ከሰባት ሚሊዮን በላይ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው፣ 1.5 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ወደ ጎረቤት ሀገራት መሰደዳቸውን ገልጿል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG