በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት ከሩሲያ ድጋፍ ለማግኘት እየጣረ መሆኑ ተነገረ


የሩሲያ የጦር መርከብ በፖርት ሱዳን እአአ 28/2021
የሩሲያ የጦር መርከብ በፖርት ሱዳን እአአ 28/2021

ከምዕራብ ሀገራት ያገኝ የነበረው የገንዘብ ድጋፍ የተቋረጠበት የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት ከሩሲያ ድጋፍ ለማግኘት እየጣረ መሆኑ ተዘገበ።

የሱዳን ጦር አዛዥ ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ ሂምድቲ፣ ሩሲያ ዩክሬንን በወረረችበት እና ዓለም አቀፉ ወግዘት በበረታበት በትናንናው ዕለት በሞስኮ በመገኘት በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ ተነጋግረዋል።

ሳመህ ሳልማን የተባሉ የምጣኔ ኃብት ተንታኝ የሂምደቲ የሞስኮ ጎብኝት በምጣኔ ሃብት ቅውስ ውስጥ ከምትገኘው ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር መታየት አለበት ባይ ናቸው። ዩናይትድ ስቴትስ እና ምዕራብ ሀገራት ይሰጡት የነበረውን የገንዘብ ድጋፍ ካቋረጡ እና የሱዳንን ብድር ለመሰረዝ ያስተላለፉት ውሳኔ ከሰረዙ ወዲህ የሱዳን ምጣኔ ኃብቷ ይዟታ በእጅጉ ተዳክሟል።

የሀገሪቱ መገበያ ገንዘብ ከዶላር ጋር ያለው ንጽጽር እየሰፋ በመጣበት በአሁኑ ሰዓት በሀገሪቱ ውስጥ ያለው የሸቀጦች ውድነት ከቀዳሚዎቹ መካከል ሆኗል።

ዩናይትድ ስቴትስ ጀነራል ሂምደቲን እና ጄኔራል አብድል ፈታ አልቡራንን በመሰሉ የጦር አመራሮች ላይ ድንገት ማዕቀቦች ከጣለች በሚል፣ ሱዳን የሩሲያን ድጋፍ ለማግኘት እየጣረች ሊሆን እንደሚችል ሳልማን ጠቁመዋል።

ካሜሮን ሀድሰን የተባሉ አትላንቲክ ካውንስል በተባለ ተቋም ውስጥ የሚሰሩ የአፍሪካ ጉዳዮች ተንታኝ በበኩላቸው የአሁኑ የሱዳን እና ሩሲያ ግንኙነት ከኢኮኖሚ ፍላጎት በዘለለ የስትራቴጂ ሽግሽግ ማሳያ ሊሆን እንደሚችልም ጠቁመዋል።

XS
SM
MD
LG