በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን፣ ከመጠለያ ጣቢያዎች ወጥተው በአውላላ መንገድ ዳር እየኖሩ ከነበሩት የሱዳን ስደተኞች መካከል 780 የሚኾኑት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን፣ የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር/ዩኤንኤችሲአር ለአሜሪካ ድምፅ አስታወቀ፡፡ ዓለምአቀፉ የስደተኞች ተቋም፣ ለአሜሪካ ድምፅ በኢሜይል በሰጠው ማብራሪያ፣ በፀጥታ ችግርና በአገልግሎት እጥረት ምክንያት በኢትዮጵያ መኖር አንችልም ብለው፣ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የእግር ጉዞ ከጀመሩት ስደተኞች መካከል፣ 780 የሚሆኑት ሱዳን መድረሳቸውን እና እዚያም ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ገልፆዋል፡፡ ወደ ሱዳን ሳይሻገሩ የቀሩት ደግሞ፣ በመተማ የስደተኞች መጠለያ እየኖሩ መሆናቸውን ገልፀው፣ በአካባቢው ባለው አለመረጋጋት ምክንያት ግን አገልግሎት እያገኘን አይደለም ብለዋል፡፡
መድረክ / ፎረም