በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የጭናው ጭፍጨፋ የማይካድራው ቅጥያ ነው” ቢል ለኔ ስዩም


ቢል ለኔ ስዩም
ቢል ለኔ ስዩም

በትግራዩ ጦርነት ምክንያት ተሰደው ሄዱ ከተባሉና በሱዳን የመጠለያ ካምፖች ከነበሩ ስደተኛች የተወሰኑት ከመጠለያው ወጥተው የት እንደሄዱ አላውቅም ሲል ዩኤንኤችሲአር አስታውቋል።

እነዚህ ሰዎች ስደተኛች ሳይሆኑ የማይካድራን ጭፍጨፋ የፈፀሙ የህወሓት ወጣቶች መሆናቸውን አስቀድሞ መናገሩን ያስታወሰው የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ አሁንም ከህወሓት ጋር ተቀላቅለዋል ይላል።

"ሰሞኑን በጭና የተፈጸመው እና ሴቶችና ሕጻናትን ጨምሮ ወደ ሁለት መቶ ንጹሃን የተገደሉበት ጭፍጨፋም የማይካድራው ቅጥያ ነው" ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የፕሬስ ክፍል ሃላፊ ቢል ለኔ ስዩም ዛሬ ለጋዜጠኛች ተናግረዋል።

“ሳምሪ” በመባል የሚጠሩ በህወሓት የተደራጁ ወጣቶች በማይካድራ በፈጸሙት ግድያ ከስድስት መቶ በላይ ንጹሃን ዜጎች መሞታቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ማስታወቁ ይታወሳል። ህወሓት ግን ይሄንን የጥናት ውጤት ጨምሮ ሁሉንም ውንጀላዎች አስተባብሏል።

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን ናይሮቢ ከሚገኘው ቢሯቸው ተጨማሪ መረጃ ለማግኘትና ቃለ ምልልስ ለማድርግ ሙከራ እያደረን ነው እንደተሳካልን ይዘን እንመለሳለን።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

“የጭናው ጭፍጨፋ የማይካድራው ቅጥያ ነው” ቢል ለኔ ስዩም
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:05 0:00


XS
SM
MD
LG