በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሌለበት የሞት ቅጣት የተፈርደበት የሱዳን አማፅያን መሪ ወደ ሀገሩ ተመለሰ


ሱዳን ውስጥ ከአምስት ዓመታት በፊት በሌለበት የሞት ቅጣት የተፈርደበት የሱዳን አማፅያን መሪ ወደ ሀገሩ ተመልሷል። የሱደን ወታደራዊ ጁንታ ከሀገሪቱ እንዲወጣ ቢጠይቀውም አልወጣም ማለቱ ተዘግቧል።

ያስር አርማን በደቡብ ሱዳን ላይ በሚያተኩረው የአሜሪካ ድምፅ ክፍል ሲናገር ለቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት የሱዳንን የሽግግር መንግሥት መምራት ያለበት ማነው? በሚለው ጥያቄ ላይ አጥብቂኝ ውስጥ በተገባበት በአሁኑ ወቅት ችግሩን በመፍታት ተግባር ለመርዳት ነው የመጣሁት ይላል።

የሱዳን ህዝባዊ ሐርነት ንቅናቄ ሰሜን የተባለው አንጃ ድርጅት ምክትል ሊቀ መንበር የሆነው አርማን ከ20 ዓመታት በላይ ለሆነ ጊዜ ኬንያ ወይም በሱዳኑ ብሉ ናየል ክፍለ ግዛትና በኑባ ተራራዎች አካባቢ ከቆየ በኋላ ባለፈው ቅዳሜ ካርቱም መግባቱ ታውቋል።

ገዢው ወታደራዊ ጁንታ ከሀገሪቱ እንዲወጣ የሚያዝ መልዕክት ትናንት ልኮብኛል። ነገር ግን ሀገሬ ነውና እዚህ የመቆየት ዓላማ ነው ያለኝ ብሏል አርማን።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG