በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን መንግሥት ከሸማቂ ተዋጊ ቡድን ጋር የሰላም ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ


ጄኔራል አብደልፋታህ አል ቡርሃን፣ አብደላዚዝ አል ሂሉ እና የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር የሰላም ስምምነት ሰነድ በትናንትናው እለት ከተፈራተሙ በኋላ
ጄኔራል አብደልፋታህ አል ቡርሃን፣ አብደላዚዝ አል ሂሉ እና የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር የሰላም ስምምነት ሰነድ በትናንትናው እለት ከተፈራተሙ በኋላ

የሱዳን መንግሥት በደቡባዊው የኑባ ተራሮች ክፍለ ግዛቱ ከሚንቀሳቀስ አንድ ዋና ሽምቅ ተዋጊ ቡድን ጋር ወደሰላም ስምምነት የሚያመራ ሰነድ በትናንትናው እለት መፈራረሙ ተገለጸ።

ሁለቱ ወገኖች የተፈራረሙት ሰነድ የዕምነት ነጻነት ለዜጎች ሁሉ የሚያረጋግጥ እና ሃይማኖትን እና የመንግሥት አስተዳደርን የሚለይ የሰላም ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስችል አንድ ርምጃ መሆኑ ተነግሮለታል።

ሰነዱ መፈረሙ በጄኔራል አብደልፋታህ አል ቡርሃን የሚመራው የጋራ ሥልጣን መንግሥት በሀገሪቱ ዙርያ ከሚንቀሳቀሱ አማጺ ቡድኖች ጋር ስምምነት በመፍጠር በሀገሪቱ ለአያሌ ዓመታት ለብዙ ሚሊዮን ሰዎች መፈናቀል እና ብዙ መቶ ሽህ ሰዎች መገደል ምክንያት የሆኑትን ግጭቶች ለማክተም በያዘው ጥረት አንድ ዋና ርምጃ ተደርጎ ታይቷል።

የሱዳን መንግሥት እአአ በ2020 በዳርፉር የሚንቀሳቀሱ ቡድኖችን ጨመሮ ከበርካታ ሽምቅ ተዋጊ ቡድኖች ጋር ስምምነት ላይ መድረሱ ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG