በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን ከ450 በላይ ቤቶች በዝናም ወደሙ


በሱዳን ሰሜናዊ ክፍል በጣለ ከባድ ዝናም፣ በሱዳን ኦምዱርማን ከባድ ዝናሙን ተከትሎ አውራ ጎዳናዎች በጭቃ እና በጎርፍ በመያዛቸው ተሽከርካሪዎች መተላለፊያ ተቸግረዋል፡፤ እአአ ነሃሴ 5/2023
በሱዳን ሰሜናዊ ክፍል በጣለ ከባድ ዝናም፣ በሱዳን ኦምዱርማን ከባድ ዝናሙን ተከትሎ አውራ ጎዳናዎች በጭቃ እና በጎርፍ በመያዛቸው ተሽከርካሪዎች መተላለፊያ ተቸግረዋል፡፤ እአአ ነሃሴ 5/2023

በሱዳን ሰሜናዊ ክፍል በጣለ ከባድ ዝናም፣ ከ450 በላይ ቤቶች እንደወደሙ፣ የአገሪቱ ብሔራዊ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

የዝናሙ ወቅት፣ በጦርነት እየታመሰች ያለችውን ሀገር ችግሮች የበለጠ ያባብሳል፤ ሲሉ፣ የረድኤት ድርጅቶች ያሰሙትን ስጋት ትክክለኛነት ያሳያል፤ ሲል፣ የኤኤፍፒ ዜና ወኪል ዘግቧል።

ከግብጽ እና ከሊቢያ ጋራ የሚዋሰነው በረሓማ አካባቢ፣ ለረጅም ጊዜያት ዝናም አግኝቶ አያውቅም፡፡

ባለፉት አምስት ዓመታት ግን፣ ከባድ ዝናም በመጣል ላይ እንደኾነ፣ የመንግሥቱ ዜና ወኪል ሱና አስታውቋል።

ዝናሙ፣ 464 ቤቶቹን ማውደሙንም፣ ዜና አገልግሎቱ ገልጿል።

የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ፣ ቀድሞውንም ርዳታ ለማድረስ በሚያዳግቱ አካባቢዎች፣ የኮሌራ እና የኩፍኝ ወረርሽኝ እንደተከሠተ አስታውቋል።

በካርቱም፣ ሰዎች በብዛት በሚኖሩባቸው አካባቢዎች፣ ዛሬ ሰኞ፣ የሮኬት እና የከባድ መሣሪያ ድብደባ እንደነበር ነዋሪዎች ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG