በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር አልባሽር ኳታርን ሊጎበኙ ነው


የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አልባሽር
የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አልባሽር

የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር አልባሽር - ሀገራቸውን በሥፋት የናጠው ፀረ መንግሥት ሰልፍ ከጀመረ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ ኳታርን ሊጎበኙ ተዘጋጅተዋል።

የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር አልባሽር - ሀገራቸውን በሥፋት የናጠው ፀረ መንግሥት ሰልፍ ከጀመረ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ ኳታርን ሊጎበኙ ተዘጋጅተዋል።

በነገው ዕለትም የሁለቱን ሃገሮች ግንኙነት ለማጠናከር ከኳታሩ ኤሚር ሼህ ታሚም ቢን ሐማድ አል ታኒ ጋር ተገናኝተው ይመክራሉ ሲል የኳታር ዜና አገልግሎት ትናንት ዘግቧል።

ባሻር እየተካሄደ ያለውን ፀረ መንግሥት እንቅስቃሴ “ለተቃውሞው የባዕዳን ወኪሎችና ሠርጎ ገቦች እጅ አለበት” ሲሉ በመከራከር ሊያጣጥሉት ሞክረዋል።

ከትላንት በስቲያ ዕሁድ ሲናገሩም “የተቃውሞ ሰልፈኞችን የሚገድሉ አንዳንድ ሰዎች በመካከላቸው ይገኛሉ” ብለዋል የሱዳኑ መሪ።

ሱዳን በከፍየኛ ሕዝባዊ ተቃውሞ የተዋጠችው መንግሥት ባለፈው ወር በዳቦ ዋጋ ላይ ጭማሪ በማድረጉ መሆኑ ተዘግቧል። በዚሁ ምክንያትም ተቃውሞው በስፋት አድጎ30 ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆዩት ፕሬዚዳንት ኦማር አልባሽር እንዲወርዱ እስከ መጠየቅ ደርሷል።

በተቃውሞ ሰልፉ ወቅት 24 ሰዎች መገደላቸውን መንግሥት ያረጋገጠ ቢሆንም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ግን በአስተማማኝ ዘገባዎች መሠረት ቁጥሩ ከተጠቀስው ዕጥፍ ይሆናል ብሏል።

ብዛት ያላቸው ሰልፈኞች ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን እንዲሁም የመንግሥቱ ፀጥታ ኃይሎች ጉዳት የደረሰባቸውን ሲያሳድዱ ሆስፒታል ውስጥ አስለቃሽ ጋዝና ጥይት መተኮሳቸውን የሚገልፁ ዘገባዎችም ወጥተዋል።

ጋዜጠኞችን የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎችን ሰልፈኞችንና የሲቪክ ማኅበረሰብ አባላትን ጨምሮ ከ8መቶ በላይ ሰዎችም ተይዘው መታሠራቸው ታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG