በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሱዳናውያን የመፈንቅለ መንግሥቱን በመቃወም አደባባይ ወጡ


በሺዎች የሚቆጠሩ የሱዳን ተቃዋሚ ሰልፈኞች በሃገሪቱ መዲና ካርቱምና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የጥቅምቱን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት በመቃወም ትናንት ሰኞ አደባባይ መውጣታቸው ተነገረ፡፡

ተቃውሟቸውን ለማሰማት ወደ ቤተመንግሥቱ አካባቢ ያመሩትን ለመበትን ፖሊስ አስለቃሽ ጋዝ መጠቀሙን ተቃዋሚዎቹ ተናግረዋል፡፡

የአሶሼይትድ ፕሬስ ዘገባ እንዳመለከተው የተቃውሞ ሰልፎቹ ከካርቱም ውጭም በከሰላ፣ በሰና፣ እና በፖርት ሱዳን ከተሞች ተካሂደዋል፡፡

የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት እኤአ ጥቅምት 25 ሥልጣን ገልብጦ በመውሰድ በርካታ የሽግግሩን መንግሥት ባለስልጣናት ያሰረ መሆኑ ይታወቃል፡፡

እኤአ በሚያዝያ 2019 የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽርን ለማስወገድ ከተደረገው ህዝባዊ አመጽ ወዲህ በሱዳን የመፈንቅለ መንግሥት ሲካሄድ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑም በዘግባው ተገልጿል፡፡

ጀኔራል አቡዱል ፈታ ከሥልጣን አስወገደዋቸውና አስረዋቸው የነበሩትን ጠቅላይ ምኒስትር ወደ ሥልጣን የመለሱ ቢሆንም የተደረገውን ድርድር ተቃሚዎቹ አልተቀበሉትም፡፡

ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ትናንት ሰኞ በያዟቸው መፈክሮች ከወታደሩ ክፍል ጋር ከእንግዲህ “ምንም ድርድር አያሰፈልግም፣ ምንም ዓይነት መቻቻልም ሆነ የሥልጣን ክፍፍል አያስፈልግም” የሚሉት እንደሚገኙበት ተዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG