ዋሽንግተን ዲሲ —
ዛሬ በአስርሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን በመላው አገሪቱ በሚገኙ ከተሞች፣ ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ፣ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስቱን በማውገዝ፣ የሲቪሉ መንግስት ወደ ቦታው እንዲመለስ ጠይቀዋል፡፡
በካርቱም በርካታ የታጠቁ የጸጥታ ኃይሎች የሚታዩ ሲሆን ፣ የተቃውሞ ሰልፉ በተጀመረ ሁለት ሰዓት ጊዜ ውስጥ፣ ኦምድሩማን በተባለ ከተማ ውስጥ፣ ሁለት ሰዎች በጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን፣ የሱዳን ዶክተሮች ኮሚቴ አስታውቋል፡፡
ምንም እንኳ በአገሪቱ የኢንተርኔት አገልግልቶ የተቋረጠ ቢሆንም አዘጋጆቹ የተቃውሞ ሰልፉን ማስተባበር መቻላቸው ተመልክቷል፡