በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን ረሃብ እየተስፋፋ ነው ተባለ


ፎቶ ፋይል፡- በሰሜን ዳርፉር የሚገኘው ዛምዛም የተፈናቃዮች ካምፕ
ፎቶ ፋይል፡- በሰሜን ዳርፉር የሚገኘው ዛምዛም የተፈናቃዮች ካምፕ

በጦርነት ትርምስ ውስጥ ባለችው ሱዳን ረሃብ በአምስት አካባቢዎች መስፋፋቱና ወደ ሌሎች ተጨማሪ አምስት አካባቢዎችም ሊስፋፋ እንደሚችል አንድ በዓለም ደረጃ ረሃብን የሚከታተል ተቋም አስታውቋል።

በጦርነቱ የሚሳተፉ ወገኖች፣ በዓለም ትልቁ የረሃብ ቀውስ እንደሆነ ለሚነገረው የሱዳን ቸነፈር ተጠቂዎች ሰብአዊ ርዳታን ለማድረስ የሚደረገውን ጥረት ማስተጓጎል መቀጠላቸውን ተቋሙ ጨምሮ አስታውቋል።

‘የረሃብ ክትትል ኮሚቴ’ በሚል የሚታወቀው ተቋም ጨምሮ እንደገልጸው፣ ከበባ ውስጥ ባለችው የሰሜን ዳርፉር መዲና አል ፋሽር ውስጥ በሚገኙ ሁለት መጠለያዎች፣ እንዲሁም በደቡብ ኮርዶፋን ግዛት በሚገኙ ሌሎች ሁለት አካባቢዎች ረሃብ ተስፋፍቷል።

ባለፈው ነሐሴ በሰሜን ዳርፉር ዛምዛም መጠለያ የተከሰተው ረሃብ መቀጠሉንም ኮሚቴው አስታውቋል።

የረሃብን ሁኔታ የሚያረጋግጠውና ደረጃ የሚያወጣው ተቋም እንዳስታወቀው፣ በሰሜን ዳርፉር ባሉ ሌሎች አምስት አካባቢዎችም ረሃቡ እንደሚስፋፋ ግምቱን አስቀምጧል። በመላ ሱዳን የሚገኙ አስራ ሰባት አካባቢዎች ደግሞ ለረሃብ ተጋላጭ መሆናቸውም ታውቋል።

በሱዳን 24፡6 ሚሊዮን የሚሆነው ወይም ከአጠቃላይ ሕዝቡ ግማሽ የሚሆነው እስከሚቀጥለው ወር ድረስ አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ እንደሚሻ ኮሚቴው አስታውቋል።

ኮሚቴው በሱዳን የሚያደርገውን የምግብ ዋስትና ጥናት መንግስት እያስተጓጎለበት እንደሆነ ገልጿል። የሱዳን መንግሥትም የኮሚቲው ሪፖርት “ተአማኒ አይደለም” በሚል በጥናቱ መሳተፉን እንዳቆመ አስውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG