በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች እንዲለቀቁ አዘዙ


ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር
ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር

የሱዳኑ መንግሥታዊ ዜና አገልግሎት /SUNA/ ዛሬ እንደዘገበው፣ ፕሬዚዳንቱ ኦማር ሀሰን አልበሽር ሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ እንዲለቀቁ ትዕዛዝ አስተላለፉ።

የሱዳኑ መንግሥታዊ ዜና አገልግሎት /SUNA/ ዛሬ እንደዘገበው፣ ፕሬዚዳንቱ ኦማር ሀሰን አልበሽር ሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ እንዲለቀቁ ትዕዛዝ አስተላለፉ።

ዘገባው እንዳመለከተው፣ ይህ ፀረ መንግሥት እንቅስቃሴዎችን ተከትሎ በርካታ ተቃዋሚዎች ከታሰሩ በኋላ ይፋ የሆነው “የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ” ትዕዛዝ፣ ሀገሪቱ ውስጥ የተጀመረው የብሔራዊ እርቅና የብሔራዊ መግባባት አካል ነው።

የሆነ ሆኖ ግን ዘገባው፣ የሚፈቱትን የፖለቲካ እስረኞች ቁጥር ይፋ አላደረገም።

ሱዳን ውስጥ የተከሰተው ከፍተኛ የኢኮኖሚ ውድቀት፣ ሀገሪቱ ውስጥ ለተቀሰቀሱት ሕዝባዊ አመፆች ዋና ምክንያት ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል።

ፕሬዚዳንት በሽር ባለፈው ወር ሰማኒያ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ማዘዛቸው አይረሳም። ተቃዋሚ ቡድኖች በሰጡት ቃል፣ ታዋቂ ፖለቲከኞችንና የሱዳኑን ኮምኒስት ፓርቲ መሪ ሙሐመድ ሙክታር አል ከሃቲቤን ጨምሮ፣ ሃምሳ እስረኞች ገና እንዳልተፈቱ ተናግረዋል።

ዩናይትድ ስቴትስና ሱዳን ውስጥ የሚገኙ የአውሮፓ ኤምባሲዎች፣ ሀገሪቱ ውስጥ የሚናገሩት እስረኞች በሙሉ እንዲፈቱ ጠይቀው ነበር ተብሏል። የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ በበኩሉ፤ ብዙዎቹ እስረኞች፣ ኢሰብዓዊ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ገልፆ ነበር።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG