በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኻርቱም ከአቢዬይ እንድትወጣ እየተጎተጎተች ነው

የሰሜን ሱዳን ጦር አቢዬይ ከተማን በኃይል መያዙ ያስቆጣቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳናዊያን ሰኞ ግንቦት 15 ቀን 2003 ዓ.ም ጁባ ከተማ ውስጥ ያደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ
የሰሜን ሱዳን ጦር አቢዬይ ከተማን በኃይል መያዙ ያስቆጣቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳናዊያን ሰኞ ግንቦት 15 ቀን 2003 ዓ.ም ጁባ ከተማ ውስጥ ያደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ

የሱዳን መንግሥት አቢዬይ ላይ ጦር አዝምቶ በኃይል መቆጣጠሩ የሰላሙን ሂደት እንደሚያወሣስበው እየተነገረ ነው፡፡

የሱዳን መንግሥት አቢዬይ ላይ ጦር አዝምቶ በኃይል መቆጣጠሩ የሰላሙን ሂደት እንደሚያወሣስበው እየተነገረ ነው፡፡

ኻርቱም የይገባኛል ጥያቄው በበረታበት አቢዬይ ግዛት ውስጥ የሚኖሩ የደቡብ ሰዎችን በኃይል አባርራ ሰሜን ዘመም በሆኑ ከቦታ ቦታ እየተንቀሣቀሱ በሚኖሩ ሰዎች ለመሙላት ዘመቻ እያካሄደች ነው ሲሉ የደቡብ ሱዳን ባለሥልጣኖች እየከሰሱ ነው፡፡

በስፋቷ በአፍሪካ ግዙፏ ሃገር የፊታችን ሐምሌ ለሁለት ለመከፈል እየተዘጋጀች ባለችበት በዚህ ወቅት በነዳጅ ሃብት በበለፀገው አቢዬይ ክፍለሃገር ላይ ያለው የይገባኛል እሰጥ አገባና መራር ትንቅንቅ የውጥረቱ ሁሉ እምብርት ሆኗል፡፡

የሱዳን መንግሥት የአቢዬይን ዋነኛ ከተማ በጦር ኃይል በጉልበት መያዙ በጎረቤታሞቹ መካከል የሚደረገውን ዓለምአቀፍ የሰላም ጥረት እያወሳሰበው እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡ ሁለቱ የፀብና የባላንጣነቱን መንገድ የመረጡ ይመስላሉ፡፡

ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ

XS
SM
MD
LG