በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ለቀቁ፣ በተቃውሞው ሁለት ሰዎች ተገደልዋል ተባለ


የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ
የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ

የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ትናንት እሁድ ሥልጣናቸውን የለቀቁ መሆናቸውን መግለጻቸው ሱዳንን የበለጠ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ የከተታት መሆኑ ተገለጠ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዶክ ከሥልጣናቸው የለቀቁት በሱዳን ሰላማዊ ሽግግርና ዲሞክራሲን ማምጣት የሚያስችል ዋስትና መስጠት ባለመቻላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ባለፈው ጥቅምት በወታደራዊ መንግሥት ግልበጣ ከሽግግሩ መንግስት ተወገደውና በቁም እስር ከቆዩ በኋላ እንደገና ወደ ሥልጣናቸው ተመልሰው የነበሩት ጠቅላይ ሚንስትሩ ከሥልጣን የመልቀቅ ውሳኔያቸውን ያሳወቁት ከወራት በኋላ ነው፡፡

በሌላም በኩል በሱዳን የሚካሄደው የዴሞክራሲ ደጋፊዎች ተቃውሞ አሁንም የቀጠለ ሲሆን በትናንትናው እለት ሁለት ሰዎች መገደላቸውን የሀኪሞች ማኅበር አስታወቋል፡፡

መፈንቀለ መንግሥቱ ከተደረገ በኋላ በቀጠለው ተቃውሞ እስካሁን 56 ሰዎች መገደላቸው ተዘገቧል፡፡

ጄኔራል አልቡርሃን የሚመሩት የሱዳን የልዕልና ምክር ቤት ባለፈው ዓርብ በሰጠው መግለጫ ሀሙስ እለት የተካሄደውን ተቃውሞ ተከትሎ የተነሳውን አመጽ አውግዞ ማንም ሰው ከህግ ውጭ ባለመሆኑ ጸጥታ አስከባሪው ኃይል ሁሉንም የህግና ወታደራዊ እምርጃዎችን እንዲወስዱ መታዘዙን አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG