በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን አውሮፕላን ተከስክሶ ዘጠኝ ሰዎች ሞቱ


በምሥራቅ ሱዳን፣ አንድ የሕዝብ ማመላለሻ አንቶኖቭ አውሮፕላን ተከስክሶ፣ አራት ወታደሮችን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎች እንደሞቱ፣ የአገሪቱ ሠራዊት አስታውቋል። አንድ ሕፃን ግን፣ ከአደጋው መትረፉን፣ ሠራዊቱ አክሎ ገልጿል።

አደጋው የደረሰው፣ በአገሪቱ ሠራዊት እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል የሚካሔደው ውጊያ፣ 100ኛ ቀኑን በያዘበት ወቅት ነው። ግጭቱ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን አፈናቅሏል።

በሱዳን የኖርዌይ ስደተኞች ም/ቤት ሓላፊ ዊሊያም ካርተር፣ “ጦርነቱ መቶ ቀን ሞላው፤ በሰው ሕይወት እና በመሠረተ ልማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡ ከዚኽ የከፋው ቀን ግን ከፊታችን ተደቅኗል፤” ሲሉ፣ ለአሶሺዬትድ ፕረስ ተናግረዋል። ሓላፊው፣ “ጦርነቱ በአጠቃላይ ቀጣናውን የማውደም ዐቅም አለው፤” ሲሉም ተደምጠዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG