ዋሽንግተን ዲሲ —
ሱዳን ውስጥ በምዕራብ ኮርዶፋን ከፍለ ግዛት ውስጥ ከአገልግሎት ውጭ የነበረ አንድ የወርቅ ማዕድን ማውጫ በመደርመሱ በውስጡ የነበሩ 38 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ፡፡
የመንግሥት የሆነው የማዕድን ኩባንያ ትናንት በሰጠው መግለጫ ከሱዳን 700 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ስፍራ አገልግሎት መስጠት ካቆመ የቆየ ሲሆን የመደርመስ አደጋው የደረሰበት ትናንት ማክሰኞ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ድርጅቱ ስፍራው ከመች ጀምሮ አገልግሎት መስጠት እንዳይቆመ ባልይገልጽም ጉዳት የደረሰባቸው ሠራተኞች በራሳቸው ፈቃድ በቦታው የተገኙ መሆኑን አስታውቋል፡፡