በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን ወታደራዊ አዛዥ አዲስ የመንግስት ምክር ቤት አቋቁሙ


የሱዳን ከፍተኛው ወታደራዊ አዛዥ ጀኔራል አብዱል ፈታ አል ቡርሃን
የሱዳን ከፍተኛው ወታደራዊ አዛዥ ጀኔራል አብዱል ፈታ አል ቡርሃን

የሱዳን ከፍተኛው ወታደራዊ አዛዥ፣ ጀኔራል አቡዱል ፈታ አልቡርሃን ፣ ከሁለት ሳምንት በፊት በሲቪል መንግሥት ላይ የተካሄደውን ወታደራዊ ግልበጣ ተከትሎ በሥልጣን ላይ የሚቆዩበትን እርምጃ በመውሰድ፣ በራሳቸው የሚመራ አዲስ ምክር ቤት ማቋቋማቸውን ትላንት ሀሙስ አስታውቀዋል፡፡

ጀኔራል አብዱል ፈታ አልቡርሃን እኤአ ጥቅምት 25 ወታደራዊ ግልበጣውን ካካሄዱ በኋላ ሥልጣንን ለሲቪል አስተዳደር እንደሚያስረክቡ በተደጋጋሚ የገቡትን ቃል መጣሳቸው በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ተቃውሞ አስነስቷል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ጉዳይ አሳስቢ መሆኑን ገልጸው የጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክን የቤት ውስጥ እስርን ጨምሮ በእስር ላይ ያሉ ሌሎች የፖለቲካ ሰዎችና መሪዎች እንዲለቀቁ ማየት እንፈልጋለን ብለዋል፡፡

ወታደራዊ ግልበጣው ከተካሄደ ጀምሮ ተቃዋሚዎችና አክቲቪስቶችን ጨምሮ ከ100 በላይ የመንግሥት ባለሥልጣናትና የፖለቲካ ሰዎች ታስረዋል፡፡

የተወሰደው እምርጃ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብና የሚይሳዝንና የዲሞክራሲ ደጋፊ የሆኑ ሱዳናውያንን ሊያስቆጣ እንደሚችልም በአሶሼትይድ ፕሬስ ዘገባ ተመልክቷል፡፡

ነገ ቅዳሜ በሲቪሎች የሚመራው የሽግግር መንግስት ወደቦታው እንዲመለስ የሚጠይቅ፣ በሱዳን ነጻነት ኃይሎች የተጠራ፣ ሌላ ትልቅ የተቃውሞ መኖሩ ተነግሯል፡፡

በአገሪቱ የተቋረጠው የኢንተርኔት አገልግሎት ተመልሶ እንዲከፈት በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የሱዳን ፍርድ ቤት አዟል፡፡ ይሁን እንጂ ኢንተርኔት አሁንም እንደተቋረጠ ነው፡፡

ከቀድሞ የሲቪል አስተዳደር ተመልሰው፣ በጀኔራል አቡዱል ፈታ አዲስ ተቋቁሟል በተባለው በአዲሱ የሽግግር መንግስት ውስጥ የተካተቱ ሶስትት ጀኔራሎችና ሌሎች ሲቪሎች መኖራቸው ተነግሯል፡፡

ካርቱም የሚገኘው ጋዜጠኛ ማይክል አቲት ለቮኤው ዘጋቢ ጀምስ ባቲ በምክር ቤቱ የተካተቱት ሲቪሎቹ መሪዎች ቀደም ሲል በጁባ የተካሄደውን ስምምነት ተከትሎ በቀደመው ምክር ቤት ውስጥ ተካተው የነበሩ መሆኑን ተናግሯል፡፡

ከቀድሞው ምክር ቤት ውስጥ በአዲሱ የተካተቱ ፣ከጀኔራል አቡድል ፈታ ቀጥሎ ምክትላቸው መሀመድ ሀምዳን፣ ሸምሰዲን ካባሺ፣ ያስሪ ዱርሃማን ፣ ሀሰን አልዳ እና መሃዲ ኢብራሂም ጃቢር መሆናቸውን አቲት ገልጿል፡፡

አዲሱን አስተዳደር በሱዳን ያሉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ይቀብሉት ይሆን ተብሎ የተጠየቀየው ማይክል አቲቲ የሚክተለውን ብሏል

“ምንም እንኳ በይፋ ከነጻነትና የለውጥ ኃይሎች አባላት በይፋ የወጣ መግለጫ ባይኖርም ይህ የሚቀበሉት መልካም ዜና ነው ማለት አይቻልም፡፡ ዛሬ ወይም ነገ ሱዳንን እንዲመራ የተቋቋመው የአዲሱ ምክር ቤት አባል አለመሆናቸውን በመግለጽ ሂደቱን በማውገዝ የሚያወጡት መግለጫ መኖሩን እናይ ይሆናል፡፡”

በአዲሱ ምክር ቤት ውስጥ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ እጣ ምን ሊሆን እንደሚችልም አቲት ሲያብራራ

“ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዶክ በአዲሱ ምክር ቤት ውስጥ ተካተዋል የሚሉ ወሬዎች አሉ፡፡ ይሁን እንጂ ሀምዶክን በምክር ቤቱ ውስጥ በማካተቱ በኩል ችግር ገጥሟቸው ሀምዶክም ራሳቸው ያልተቀበሉ ሊሆን የሚችሉበት ሁኔታ ይኖራል፣ ግን ብዙ ያልታወቁ ነገሮች አሉ፡፡” ብሏል፡፡

የሱዳን የቀድሞ የባህልና ማስታወቂያ ሚኒስትር የነበሩት ሀምዛ ባሎል በወታደራዊ ኃይሉ ተይዘው ከተለቀቁ ሰዎች አንዱ ሲሆን “የትናንቱን አዲስ ምክር ቤት የማቋቋም ዜና የመፈቅንለ መንግስቱ ተቀጥላ ነው” ብለውታል፡፡

ሚኒስትሩ አያይዘውም የዴሞክራሲ አራማጅ ተቃዋሚ ሲቪሎች ከወታደራዊ ኃይሉ ጋር ለመደራደር አለመፈለጋቸው ትክክል ነው ብለዋል፡፡

በቀደመው ስምምነት እንዲቋቋም የተፈለገው ምክር ቤት በአክቲቪስቶች የተመረጡ 5 ሲቪሎች እና ከወታደሩ የተመረጡ 5 ሰዎች ሆነው ከሁለቱም ወገኖች የተመረጡ አንድ የሲቪል መሪ እንዲኖረው ነበር፡፡ አዲስ ተቋቁማል የተባለ ምክር ቤት ግን ይህን የሚያሟላ ሆኖ አልተገኘም፡፡

የአፍሪካ ህብረት፣ የአረብ ሊግና የተባበሩት መንግሥታትን ጨምሮ፣ የተለያዩ አገሮች ወታደራዊ ግልበጣውን ያወገዙ ሲሆን፣ የምዕራባዊ አገሮች ዲፕሎማቶችም ጉዳዩን ለመሸምግል ሲጥሩ ከርመዋል፡፡

በሱዳን የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ እስካሁን ቢያንስ 14 ሰዎች መገደላቸውን አሶሼይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG