በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሱዳን ተራማጅ የህግ ለውጥ አደረገች


ሱድን የሴቶችን ግርዛት ያሚያግድና ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች የአለኮል መጠጥ እንዲጠጡ የሚፈቅድ ህግ ማውጣትዋን የፍርድ ሚኒድቴር ትላንት አስታውቋል።

ይህ እርምጃ ለአራት አስርተ-አመታት ለሚጠጋ ጊዜ ያህል ዘልቆ የነበረውን የሴቶችን ነጻነት የሚገድበውን አክራሪ አስላማዊ ፖሊሲን ቀልብሷል ማለት ነው።

የሱዳኑ ሉአላዊ ካውንስል በተጨማሪም ሴቶች ከልጆቻቸው ጋር ሆነው ለመጓዝ ከፈለጉ ወንድ ከሆነ የቤተሰብ አባል ፈቃድ ማግኘት ያስፈልጋቸዋል የሚለው ህግም እንዲቀር አድርጓል።
የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብዱላ ሓምዶክ “የፍርድ ስርአቱን በማሻሳል ተግባር የተወሰደ ወሳኝ እርምጃ ነው” በማለት አሞግሰውታል።

ለሴቶች መብት የቆሙት ወገኖች ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው እርምጃ መወሰዱ እዳስደሰታቸው ገልጸዋል። ነገር ግን የሴቶች ግርዛት በህበረተሰቡ ዘንድ ስርጾ የቆየ ባህል መሆኑን በማስታወስ አስጥንቅቀዋል።

ማንኛውም በሴቶች ላይ የግርዘት ተግባር ሲፈጽም የተገኘ ስው በ 3 አመታት እስራት እንደሚቀጣ አሶሼተድ ፕረስ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

XS
SM
MD
LG