በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን መንግሥት በዓለምቀፍ የወንጀል ችሎት የሚፈለጉትን ለማስረከብ ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ


የኻርቱም፣ ሱዳን ካርታ።
የኻርቱም፣ ሱዳን ካርታ።

ባለፈው አመት በህዝባዊ አመጽ ከስልጣን ተወግደው ኻርቱም ውስጥ በእስር የሚገኙት ዐል-ባሽር ዳርፉር ውስጥ የጦርነት ወንጀል፣ ፍጅትና በስብእና ላይ ወንጀል ፈጽመዋል በሚል በአለም አቀፍ የወንጀል ችሎት ይፈለጋሉ። ዳርፉር ውስጥ በተካሄደው ግጭት በ 300,000 የሚገመቱ ስዎች አልቀዋል።

የሱዳን መንግስት አምስቱን ተጠርጣሪዎች ለአለም አቀፉ ችሎት ለማስረከብ ባለፈው የካቲት ወር ከአማጽያን ጋር የተስማማ ቢሆንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብደላ ሃምዶክ እስካሁን ባለው ጊዜ በይፋ ሳይናገሩ ቆይተዋል።

“መግስቱ በጦርነት ወንጀልና በስብና ላይ ወንጀል በመፈጸም የተከሰሱትን ለአለም አቀፉ ችሎት በማስረከ ተግባር ለመተባበር ሙሉ በሙሉ ዝግጁ መሆኑን ደግሜ እናገራለሁ”ብለዋል ሃምዶክ በቴሌቪዥን ባደረጉት ንግግር።

XS
SM
MD
LG