በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት የዳርፉሩን ሚሊሻ መሪ ጉዳይ መመልከት ጀመረ


ፎቶ ፋይል፦ የሱዳን ጃንጃዊድ ሚሊሻ መሪ የነበሩትን አሊ አብዱልረህማን
ፎቶ ፋይል፦ የሱዳን ጃንጃዊድ ሚሊሻ መሪ የነበሩትን አሊ አብዱልረህማን

ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ቀድሞ የሱዳን ጃንጃዊድ ሚሊሻ መሪ የነበሩትን አሊ አብዱልረህማንን የወንጀል ክስ ዛሬ ማክሰኞ መመልከት መጀመሩ ተነገረ፡፡

በዳርፉር ግጭት ወቅት ፈጽመውታል በተባለ 31 የጦር ወንጀልና በሰአብዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች የተከሰሱትና አቡዱልረህማን ጥፋተኛ አለመሆናቸውን መግለጻቸው ተመልክቷል፡፡

አብዱልረህማን ይመሩት የነበረው ታጣቂው የጃንጀዊድ ሚልሻ በቀድሞ የሱዳን ፕሬዛዳንት ኦማር አልባሽር የዳርፉርን አማጽያን ለመደምሰስ እኤአ በ2003 የተሰማራ ጦር መሆኑን ተገልጿል፡፡

ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት አብዱልረህማን ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ት ዕዛዙን ያወጣው እኤአ በ2007 ሲሆን ተከሳሹ ከፍርድ ቤቱ ፊት የቀረቡት እኤአ በ2020 መሆኑ ተመልክቷል፡፡ ከዚያ ጊዜ አንስቶ ኔዘርላንድ በሚገኘው ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ታስረው እንደሚገኙም ተነግሯል፡፡

በዳርፉር ግጭት ወደ 300ሺ ሰዎች መገደላቸው ሲገለጽ እኤአ እስከ 2015 ድረስ ወደ 2.7 ሚሊዮን ሰዎች መፈናቀላቸው ተመልክቷል፡፡

በአቡድልረህማን ለፍርድ መቅረብ ብዙዎች የዳርፉር ሰዎች መደስታቸውን ገልጸዋል፡፡

ዛሬ በደቡብ ሱዳን የሚኖሩት ኢብራሂም ያያ ኡስማን ለቪኦኤ ሲናገሩ

“ይህ ሰው በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት በወንጀለኝነት ከተፈረደበት ለጥፋቱ መቀጣት ይኖርበታል፡፡ እኛ ፍትህ እንፈልጋለን፡፡ የኔ ሰዎች በዳርፉ ተገድለዋል ለምን እንደተገደሉ ማወቅ እንፈልጋለን” ብሏል፡፡

XS
SM
MD
LG