በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን ከግማሽ በላይ የሚሆነው ሕዝብ የከፋ የምግብ ዋስትና ዕጦት ገጥሞታል


ፎቶ ፋይል፦ ነዋሪዎች ምግብ ለማግኘት እየተጠባበቁ፤ በኦምዱርማን፣ ሱዳን፣ እአአ መጋቢት 11/2024
ፎቶ ፋይል፦ ነዋሪዎች ምግብ ለማግኘት እየተጠባበቁ፤ በኦምዱርማን፣ ሱዳን፣ እአአ መጋቢት 11/2024

በጦርነት በመታመስ ላይ ባለችው ሱዳን 25.6 ሚሊዮን የሚሆነው ወይም ከግማሽ በላይ የሚሆነው ሕዝብ የከፋ የምግብ ዋስትና ዕጦት እንደገጠመው አንድ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የወጣ የጥናት ሪፖርት አመልክቷል።

የምግብ ዋስትናን ደረጃ የሚያወጣውና (IPC) በመባል የሚታወቀው መለኪያ እንዳመለከተው፣ 755 ሺሕ የሚሆኑ ሰዎች ረሃብ የገጠማቸው ሲሆን፣ 8.5 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል።

ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር፣ ከ 14 ወራት በፊት፣ በሁለት ጀኔራሎች መካከል በተነሳው ጦርነት ምክንያት ሱዳን ከዚህ በፊት ገጥሟት የማያውቅ የከፋ የምግብ ዋስትና ዕጦት እንደገጠማት ሪፖርቱ አመልክቷል። ባለፈው ታህሳስ ወር ከተሰራው ተመሳሳይ ጥናት ወዲህ ችግሩ በ45 በመቶ ማደጉን ሪፖርቱ አመልክቷል።

ግጭቱ ከፍተኛ የሆነ መፈናቀል ከማስከተሉና ዕርዳታ የማመላለሻ መንገዶችን ከመዝጋቱም በላይ፣ እጅግ አስፈላጊ የሁነ የሰብዓዊ ዕርዳታ ተደራሽነት ውስን እንዲሆን ማድረጉን ሪፖርቱ ጠቁሟል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG