በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የስደተኞች ቁጥር መጨመሩ ተገለጸ


ግጩትን በመሸሽ ተከዜ ወንዝን በመሻገር ወደ ሱዳን የሚሸሹ ኢትዮጵያውያን
ግጩትን በመሸሽ ተከዜ ወንዝን በመሻገር ወደ ሱዳን የሚሸሹ ኢትዮጵያውያን

የዓለም አቀፉ የቀይመስቀል ከኢትዮጵያ ትግራይ ክልል እና ከሌሎች የሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍሎች በተነሳው ጦርነት ምክንያት እጅግ ብዙ ስደተኞች እየተጨመሩ በመሆኑ ደቡብ ምስራቃዊ ሱዳን ካምፖች የስደተኞቹን የኑሮ ሁኔታ ይብሱን ከባድ እያደረገው መሆኑን አስታወቀ፡፡

አይሲአርሲ ትናንት ባወጣው መግለጫ ምግብ የንጹህ ውሃ አቅርቦት መጠለያ እና የንጽህና መጠበቂያዎች እጥረት አስከፊ ደረጃ ላይ መድረሱን የገለጸ ሲሆን በምግብ እጥረት በወባ እና ሄፐታይተስ ኢ በተሰኘው የጉበት በሽታ ዓይነት የሚጠቁ ሰዎች ቁጥርም ጨምሯል ብሏል፡፡

በአሁን ሰዓትም ወቅቱ ክረምት መሆኑ ሁኔታዎችን እንዳባባሰው እና አንዳንድ ስደተኞችም አደገኛ በሆኑ መንገዶች እንዲጓዙ ወይም ወደሃገሪቱ ሌሎች ቦታዎች እንዲንቀሳቀሱ አስገዱዷቸዋል ብሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በአብዛኛው የትግራይ ክፍል የቴሌኮሚኒኬሽን ግንኙነት ባለመኖሩ ስደተኞቹ የቤተሰቦቻቸው ሁኔታ ስጋት ውስጥ እንደከተታቸው ገልጾ ብዙዎቹም የትዳር አጋሮቻችው እና ልጆቻቸው የት እንዳሉ አለማወቃቸው የስነልቦና ችግር እና የአእምሮ ጠባሳ ፈጥሮባቸዋል ሲል አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG