በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ከኢትዮጵያ ለሱዳን የተሰጠ መሬት ስለመኖሩ የሚቀርብ ክስ፣ ልብ ወለድ ነው” ይላል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጎረቤት አገሮች ጉዳይ ሃላፊ አቶ መለስ አለም
በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጎረቤት አገሮች ጉዳይ ሃላፊ አቶ መለስ አለም

18ኛው የኢትዮ ሱዳን የድንበር ልማት ስብሰባ መቀሌ ከተማ ውስጥ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

18ኛው የኢትዮ ሱዳን የድንበር ልማት ስብሰባ መቀሌ ከተማ ውስጥ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ከኢትዮጵያ መሬት ተቆርሶ ለሱዳን ተሰጥቷል ለሚለው ከተቃዋሚ ድርጅቶች የሚቀርበውን ተደጋጋሚ ክስ ልብ ወለድ ነው ይላል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፡፡

በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጎረቤት አገሮች ጉዳይ ሃላፊ አቶ መለስ አለም ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት መግለጫ የስብሰባው ዋና ዓላማ በሁለቱም አገራት ጥቅም ዙርያ የሚነጋገር መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በኢኮኖሚና ማሕበራዊ፣ በፖለቲካና ፀጥታ፣ በጤና፣ በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ዙርያ ዝርዝር ውይይት መካሄዱን አቶ መለስ ይናገራሉ፡፡

ከኢትዮጵያ ለሱዳን ተቆርሶ የተሰጠ መሬት ስለመኖሩ ተቃዋሚ ድርጅቶች በተደጋጋሚ የሚያቀርቡትን ክስ፣ በሁለቱም አገሮች ድንበር ላይ የሚኖሩ ገበሬዎች በመሬት የባለቤትነት ጉዳይ ላይ እንደሚጋጩ ሱዳን ቱሪቡን ላቀረበው ዘገባ፣ እንዲሁም በማሕበረሰባዊ ድረ ገፅ ውይይቱ በድንበር አከላለል ዙርያ የሚደረግ ስለመሆኑ የተጻፈው በጎበዝ ፀሐፊ የተፃፈ ልብወለድ ነው ሲሉ አቶ መለስ አለም መልስ ሰጥተዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

“ከኢትዮጵያ ለሱዳን የተሰጠ መሬት ስለመኖሩ የሚቀርብ ክስ፣ ልብ ወለድ ነው” ይላል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:13 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG