ዋሺንግተን ዲሲ —
ሱዳን ከኤርትራ ጋር ያላትን ድንበር ዘግታለች።
ድንበሩ የተዘጋው የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አል በሽር በከሰላና በሰሜን ኮርዶፋን ክልሎች ለሥድስት ወራት ያህል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካወጁ በኋላ መሆኑን “ሱና” የተባለው የዜና አገልግሎት ባለፈው ቅዳሜ ገልጿል።
አዋጁ ባለፈው ጥቅምት ወር ዳርፉርና ብሉናይል አጠገብ የተጀመረው ህገወጥ አሸጋጋሪዎችን ትጥቅ ለማስፈታት የሚካሄደው ዘማቻ አካል መሆኑ ተገልጿል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ