በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኻርቱም የኦባማን መልዕክት አልተቀበለችም


የተሰጋውን የሠላም መደፍረስ ለማስቀረት የአፍሪካ ሕብረትና የመንግሥታቱ ድርጅት የልዑካን ቡድን ደቡብ ኮርዶፋን ተገኝቷል፡፡

በደቡብና በሰሜን ሱዳን መካከል የሐምሌ ሁለቱን የግዛት መከፈልና የደቡብ ሱዳን አዲስ መንግሥት ምሥረታ ያሰጋል የሚባለው የወገኖቹ ግጭቶች እንዲያበቁ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ትናንት ያስተላለፉትን ጥሪ ኻርቱም ውድቅ ማድረጓ ተዘግቧል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ወገኖቹን ለማደራደር የተያዘው ዓለምአቀፍ ጥረት ደቡብ ኮርዶፋን ግዛት ውስጥ በተነሣው ጦርነት ሣቢያ መስተጓጎሉ ቢሰማም የአፍሪካ ሕብረቱ የሰላም ተልዕኮ እዚያው ደቡብ ኮርዶፋን እንደሚገኝ ማምሻውን የደረሰን ዘገባ ጠቁሟል፡፡

ዘገባውን ያዳምጡ

XS
SM
MD
LG