በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን የጎርፍ መጥለቅለቁ እንደቀጠለ ነው


ፎቶ ፋይል፦ ከካርቱም ደቡብ ምስራቅ ሱዳን፣ በአቡድ መንደር ከከባድ ዝናብ በኋላ የደረሰ የጎርፍ መጥለቅለቅ እአአ 8/23/2022
ፎቶ ፋይል፦ ከካርቱም ደቡብ ምስራቅ ሱዳን፣ በአቡድ መንደር ከከባድ ዝናብ በኋላ የደረሰ የጎርፍ መጥለቅለቅ እአአ 8/23/2022

ከፍተኛ መጠን ያለው የወቅቱ ዝናብ በፈጠረው ጎርፍ ሳቢያ በአብዛኛው የሱዳን ክፍል ጉዳት መድረሱ እንደቀጠለ ነው። በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ቤቶችና የእርሻ መሬቶች በጎርፉ ወድመዋል።

ጎርፉ ወሳኝ የሆኑ መሠረተ ልማቶችን በማውደሙ እንደ ኮሌራ ያሉ ውሃ ወለድ በሽታዎች ወረርሽኝ እንዳይከሰት ተሰግቷል።

የተመድ እንደሚለው፣ በዚህ ዓመት ካለወቅቱ በግዜ የጀመረው ዝናብ የ258ሺህ ሰዎችን ህይወት አተራምሷል። በርካታ መንደሮች ሲጥለቀለቁ፣ ከሱዳን 18 ግዛቶች ውስጥ 15ቱ በውሃ ታጥበዋል።

የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ እንደሚለው፣ የናይል ወንዝ፣ ነጭ ናይል፣ ምዕራብ ኮርዶፋን፣ እና ደቡብ ኮርዶፋን የተባሉት ግዛቶች በጎርፉ እጅግ ተጠቅተዋል።

የማስተባበሪያ ቢሮው በአብዛኛው ህፃናትና ሴቶች የሚገኙባቸው 30 ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች ንጹህ የመጠጥ ውሃ ተደራሽነትን ለማሻሻል እየሰራ መሆኑ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG