በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን መንፈንቅለ መንግሥት መሪ “አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሾማል” አሉ


ፎቶ ፋይል፡- የሱዳን ተቃዋሚ ሰልፈኞች በአትባራ፣ ሱዳን
ፎቶ ፋይል፡- የሱዳን ተቃዋሚ ሰልፈኞች በአትባራ፣ ሱዳን

የሱዳንን መፈንቅለ መንግሥት የመሩት ወታደራዊ ጀኔራል፣ በዚህ ሳምንት አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሰይሙ አስታወቁ፡፡

የሩሲያ መንግሥት ዜና አገልግሎት ለሆነው ስፑትኒክ፣ ዛሬ ዓርብ ቃለ መጠይቅ የሰጡት ጀኔራል አብዱል ፈታ አልቡርሃን “አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከወታደራዊ ኃይል ጋር የአመራር ሥልጣን ተጋርቶ አገሪቱን የሚመራ ካቢኔ ያቋቁማል” ብለዋል፡፡

አልቡርሃን የቀድሞውን ካቢኔ አፍርሰው ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶኮና ሌሎች የመንግሥት ባለሥልጣናትና የፖለቲካ መሪዎችን ማሰራቸውይታወቃል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትና የምዕራብ አገሪመሪዎች ድርጊቱን አውግዘዋል፡፡

ወታደራዊው ኃይል በደረሰበት ዓለም አቀፍ ግፊት ሀምዶክን ባሰረ ማግስት በመፍታት ቤታቸው ሆነው በአይነቁራኛ በሚጠበቁበት ሁኔታ እንዲቆዩ ማድረጉም ይታወቃል፡፡

XS
SM
MD
LG