በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከሱዳን ወደ ደቡብ ሱዳን መሸሻቸውን ተመድ አስታወቀ


ፎቶ ፋይል፦ ተፈናቃዮች ወርሃዊ ቀለባችውን ለማግኘት የምግብ ማከፋፈያ ማዕከል እየጠበቁ ናቸው፤ በቤንቲዩ፣ ደቡብ ሱዳን
ፎቶ ፋይል፦ ተፈናቃዮች ወርሃዊ ቀለባችውን ለማግኘት የምግብ ማከፋፈያ ማዕከል እየጠበቁ ናቸው፤ በቤንቲዩ፣ ደቡብ ሱዳን

በሱዳን የሚካሄደውን ጦርነት በመሸሽ ወደ ደቡብ ሱዳን የተሻገሩት ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን በላይ ማሻቀቡን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር አስታውቋል። ይህም አስከፊ ያለውን የሰብአዊ ቀውስ እንደሚያመለክት ኮሚሽነሩ አስታውቋል።

በጦርነቱ በአሥር ሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ፣ ከ12 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል።

አንድ ሚሊዮን ከሚሆኑት ውስጥ አብዛኞቹ ደቡብ ሱዳን ውስጥ የነበረውን የእርስ በእርስ ጦርነት በመሸሽ ወደ ሱዳን ተሰደው የነበሩ መሆናቸውንና፣ አሁን ደግሞ በሱዳን ላለፉት 21 ወራት ሲካሄድ የነበረውን ግጭት ሸሽተው ወደ መጡበት ደቡብ ሱዳን የተመለሱ መሆናቸውን የስደተኞች ኮሚሽነሩ አስታውቋል።

“ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደቡብ ሱዳን መድረሳቸው እየጨመረ የመጣውን ቀውስ አሳሳቢነት የሚያመለክት ነው” ሲሉ በደቡብ ሱዳን የኮሚሽነሩ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።

ሱዳን በዓለም እጅግ የከፋ መፈናቀል የሚታይባትና በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍልም ረሃብ የታወጀባት ሃገር ሆናለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG